TIKVAH-SPORT
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469
- 24 hours
- –
- 7 days
- –
- 30 days
- –
- Reactions
- 326
- Reposts
- 5
- Comments
- 19
Subscriber growth
We started tracking this channel recently; the chart fills in day by day.
TIKVAH-SPORT has 291,894 subscribers. A typical post is seen by about 46,322 people within a day, an engagement rate of 15.9%.
Views as a post ages
Average views at each age, posts of the last 30 days.
- 3 h
- 30.5K
- 6 h
- 45.4K
- 24 h
- 46.3K
When it posts
Times in UTC. 29 posts in 90 days.
Recent posts
-
የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች የት ይካሄዳሉ ? ስፔን እና ፈረንሳይ የኔሽንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። ስፔን በሳንቲያጎ በርናቦ እና ቫላዶሊድ ስታዲየም ጆሴ ዞሪላ ጨዋታዎቹን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባለች። ፈረንሳይ በበኩሏ ከኦሎምፒክ ሊዮን እና ሴንት ኢቴን ጋር በመሆን ለማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረቧ ተገልጿል። ጨዋታዎቹ የት እንደሚካሄዱ ቀጣይ ሳምንት አርብ እንደሚወሰን ማርካ ዘግቧል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ፖቼቲኖ የቡድኑን እረፍት ቀን ይሰርዛሉ ! የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በቀጣይ ከጨዋታ ማግስት የእረፍት ቀን እንደማይኖራቸው ተገልጿል። ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከጨዋታ ማግስት ተጨዋቾቹን ልምምድ ማዕከል ማግኘት እንደሚፈልጉ ዘ ሰን ዘግቧል። አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ በቀጣይ ስራቸው የቡድኑን አካል ብቃት ማሻሻል እንደሚፈልጉ ተነግሯል። ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር አመት በአካል ብቃት ደረጃ ደካማ ቁጥር አስመዝግቧል። ክለቡ ቦታዎችን በማካለል ከሊጉ 19ኛ ደረጃ ሲይዝ በአካይ ፍጥነት በተመሳሳይ 19ኛ ደረጃ ይዟል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ለበርካታ አመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት የምናውቀው የአባይ ቲቪ ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ ከከባድ ህመም ጋር እየታገለ ይገኛል። ጋዜጠኛው የኩላሊት ህመም ገጥሞት በህክምና ተቋም በመተኛት እንዲሁም እየተመላለሰ ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል። ህመሙ የማንኛውንም ሰው አቅም እንደመፈታተኑ ብሎም እስከ ንቅለ ተከላ ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚፈልግ ለጋዜጠኛው የድጋፍ ጥሪ ቀርቧል። ጋዜጠኛ ዮሴፍ ለሀገር ውስጥ ስፖርት ብሎም ለሙያው የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው። የድጋፍ ገንዘቡ ገቢ የሚደረገው በባለቤቱ ወ/ሮ ብርሃን በክረፂዮን የሂሳብ ቁጥር አካውንት ነው። ኢ/ን/ባንክ :- 1000729159895 - ወይዘሮ ብርሃን በኩረፅዮን @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ሰባት ቁጥር ማልያን ማን ይለብሳል ? ፖርቹጋል ዛሬ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ራሱን ካገለለ በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከዴንማርክ ጋር ታደርጋለች። በጨዋታው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ይለብሰው የነበረውን ሰባት ቁጥር ማልያ ካርሎስ ፎርብስ ለብሶ ይጫወታል። ካርሎስ ፎርብስ ባለፈው አመት የፖርቹጋል የመጀመሪያ ጨዋታውን በ ሰባት ቁጥር ማልያ ነበር ያደረገው። በቅርቡ የሰባት ቁጥር ማልያውን ራፋኤል ሊያኦ ለብሶ ሲጫወት…
-
⚽️ የስፖርት ዜናዎችን በትኩሱ ያግኙ! 💬 ከሳፋሪኮም ቁጥራችን ወደ *799# በመደወል አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2ብር ብቻ! #SafaricomEthiopia #Furtheraheadtogether
-
ገደቡ ለማይበግራቸው ለታላላቅ ቡድኖች ትክክለኛው ምርጫ 🚚ከዴሊቨሪ ጋር 👏 የምርት ጥራቱን የኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ብሄራዊ ቡድን የመሰከሩለት 📞ለማዘዝ 8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣ +251901138283 +251901836858 +251901835855 🛒ወይም በቀጥታ👇ይህን በመጫን https://t.me/m/I3tmfKJ0ZDJk ⭐️ #ከዋናው_ማዘዝ_ቀላል_ነው!
-
“ ከዳኛ ጋር መጫወት ከባድ ነው “ ራፊና በዛሬው የብራዚል እና ጃፓን ጨዋታ ቀይ ካርድ የተመለከተው ራፊና በጨዋታው ዳኛ መበሳጨቱን ገልጿል። “ ይህንን ሁሉ የዳኝነት ስህተት እየተመለከቱ መረጋጋት ያዳግታል “ ሲል ራፊና ተናግሯል። “ ዳኛውን ለማነጋገር ብዙ ጊዜ ጥረት አድርጊያለሁ “ ያለው ራፊና “ እሱ እኔን ለመስማት ፍቃደኛ አይደለም ብሏል። አክሎም “ ከዳኛ ጋር መጫወት ከባድ ነው “ ሲል ተደምጧል። ራፊና ቀይ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቀጣይ የወዳጅነት ጨዋታ አይሰለፍም። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ጃፓን ብራዚልን አሸንፋለች ! በአለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ጃፓና ብራዚልን 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። የጃፓንን የማሸነፊያ ግቦች ሳካሞቶ ፣ ናካሙራ እና ኩቦ ማስቆጠር ችለዋል። ቪንሰስ ጁኒየር የብራዚል ብሔራዊ ቡድንን ሁለት ግቦች ከመረብ አሳርፏል። በጨዋታው ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው ራፊና እና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። ራፊና ቀይ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቀጣይ ከ ሲንጋፖር ጋር በሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ አይሳተፍም። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ አስፈርሟል ! ማንችስተር ዩናይትድ የእንግሊዝ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ታይለር አጃይን ዝውውር አጠናቀዋል። የ 16ዓመቱ ተጨዋች ታይለር አጃይ ሪዲንግን በመልቀቅ ማንችስተር ዩናይትድን ተቀላቅሏል። ታዳጊው በሶስቱም የፊት መስመር ቦታዎች የሚጫወት ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ እንደ ዘጠኝ ቁጥር ተጨዋች ይመለከተዋል ተብሏል። ተጨዋቹ በቀጣይ በዳረን ፍሌቸር የሚመራውን ማመንችስተር ዩናይትድን ከ 18ዓመት በታች ቡድን ይቀላቀላል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ሰባት ቁጥር ማልያን ማን ይለብሳል ? ፖርቹጋል ዛሬ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ራሱን ካገለለ በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከዴንማርክ ጋር ታደርጋለች። በጨዋታው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ይለብሰው የነበረውን ሰባት ቁጥር ማልያ ካርሎስ ፎርብስ ለብሶ ይጫወታል። ካርሎስ ፎርብስ ባለፈው አመት የፖርቹጋል የመጀመሪያ ጨዋታውን በ ሰባት ቁጥር ማልያ ነበር ያደረገው። በቅርቡ የሰባት ቁጥር ማልያውን ራፋኤል ሊያኦ ለብሶ ሲጫወት ነበር። የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በውድድሮቹ ላይ ከአንድ እስከ ሀያ ስድስት ያሉ ቁጥሮች ግዴታ እንዲለበሱ ያስገድዳል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
“ ማንችስተር ዩናይትድን ማሰልጠን ለእኔ ክብር ነበር “ ማይክል ካሪክ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ትላንት ሀላፊነት ከተሰናበተ በኋላ ደጋፊዎቹን ባስተላለፈው መልዕክት ተሰናብቷል። “ የምወደውን ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ማሰልጠን ለእኔ ክብር ነበር “ ሲል ማይክል ካሪክ ተናግሯል። አክሎም “ በቅርብ ጊዜያት ውጤቱ ጥሩ ባይሆንም ፍቅር እና ድጋፍ አሳይታችሁኛል ያ ለእኔ ጨዋታ ከማሸነፍ በላይ ነው "ብሏል። “ ይሄ ፍቅር መቼም አይጠፋም ፤ ለማንችስተር ዩናይትድ ስኬት እመኛለሁ ከአሁን በኋላ ከእናንተ ጋር ነኝ አብሪያችሁ እመለከታለሁ “ ሲል ጨምሮ ተናግሯል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
የሞዛምቢክ አሰልጣኝ ከጋዜጠኞች ጋር ተጋጩ ! በኢትዮጵያ ሽንፈት የገጠማቸው ሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቺኩንሆ ኮንዴ ከጋዜጠኞች ጋር ተጋጭተዋል። አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ከጋዜጠኞች ጋር ወደ ፀብ መግባታቸው ተገልጿል። ፀቡ ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ ከጋዜጠኞች በቀረበ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን በኋላም ወደ አካላዊ ግጭት አምርቷል። አስተያየት ለመስጠት በቦታው የተገኘው የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጣልቃ ገብቶ ግጭቱን ማረጋጋቱ ተገልጿል። አሰልጣኙ ጋዜጠኛውን “ እሰብርሀለሁ “ እያሉ ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቷል። የብሔራዊ ቡድኑ የድህረ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ በሁከት መጠናቀቁን የሞዛምቢክ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ለበርካታ አመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት የምናውቀው የአባይ ቲቪ ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ ከከባድ ህመም ጋር እየታገለ ይገኛል። ጋዜጠኛው የኩላሊት ህመም ገጥሞት በህክምና ተቋም በመተኛት እንዲሁም እየተመላለሰ ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል። ህመሙ የማንኛውንም ሰው አቅም እንደመፈታተኑ ብሎም እስከ ንቅለ ተከላ ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚፈልግ ለጋዜጠኛው የድጋፍ ጥሪ ቀርቧል። ጋዜጠኛ ዮሴፍ ለሀገር ውስጥ ስፖርት ብሎም ለሙያው የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው። የድጋፍ ገንዘቡ ገቢ የሚደረገው በባለቤቱ ወ/ሮ ብርሃን በክረፂዮን የሂሳብ ቁጥር አካውንት ነው። ኢ/ን/ባንክ :- 1000729159895 - ወይዘሮ ብርሃን በኩረፅዮን @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
“ ዩናይትድን አለመቀበል ከባድ ነው “ ፖቼቲኖ ማንችስተር ዩናይትድን የተረከቡት አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኙ ዛሬ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ " አሜሪካን ለመልቀቅ መወሰን የህይወቴ ከባዱ ውሳኔ ነው “ ሲሉ በእንባ ተናግረዋል። አክለውም " እንደ ማንችስተር ዩናይትድ ያለ ትልቅ ክለብ ሲጠይቅ እድሉን ማሳለፍ ከባድ ነው “ብለዋል። “ እንደዚህ አይነት እድሎች በህይወት ውስጥ ብዙ ጊዜ የማይፈጠሩ ናቸው “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። “ ማንችስተር ዩናይትድን በመቀላቀሌ በጣም ተደስቻለሁ ነገርግን አሁን ስለእሱ ለማውራት ጊዜው አይደለም “ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ. @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
ዋልያዎቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 1ለ0 አሸንፏል። ለዋልያዎቹ የማሸነፊያ ግቡን ከነአን ማርክነህ ማስቆጠር ችሏል። ሀገራችን ኢትዮጵያ በማጣሪያ ውድድሩ የመጀመሪያ ድሏን ማስመዝገብ ችላለች። ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ማክሰኞ ባሕር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ላይ የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የምድቡ ደረጃ ምን ይመስላል ? 1ኛ. ሴኔጋል :- 7 ነጥብ 2ኛ. ሞዛምቢክ :- 4 ነጥብ 3ኛ. ኢትዮጵያ :- 3 ነጥብ 4ኛ. ሱዳን :- 3 ነጥብ @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
በውሎ ቀናችንን ፀዴ እናድርግ! 📱 በ60 ብር ብቻ ከጠዋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 12:00 የሚቆይ ውሎ ያልተገደበ ጥቅል ውሎአችንን እንደልብ እናሳልፍ እንደልብ፡፡ *777# → ኢንተርኔት → ያልተገደበ #SafaricomEthiopia #WulloUnlimited #FurtherAheadTogether
-
90+2' ሞዛምቢክ 0 - 1 ኢትዮጵያ ⚽ ከነአን @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
85' ሞዛምቢክ 0 - 1 ኢትዮጵያ ⚽ ከነአን @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
“ ላሊጋ ከፕሪሚየር ሊግ የበለጠ ቴክኒካል ነው “ ኩኩሬላ የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ማርክ ኩኩሬላ ላሊጋ ከፕሪሚየር ሊግ የበለጠ ቴክኒክ እንደሚጠይቅ ገልጿል። “ የስፔን ላሊጋ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበለጠ ቴክኒክ ይጠይቃል “ ሲል ማርክ ኩኩሬላ ተናግሯል። አክሎም “ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበለጠ አካላዊ ጥንካሬ ይጠይቃል “ ሲል ገልጿል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
-
እረፍት ሞዛምቢክ 0 - 0 ኢትዮጵያ @tikvahethsport @kidusyoftahe
Questions about TIKVAH-SPORT
How many subscribers does TIKVAH-SPORT have?
TIKVAH-SPORT (@tikvahethsport) has 291,894 subscribers as of November 14, 2026.
How many people see a post on TIKVAH-SPORT?
A typical post gets about 46,000 views within 24 hours, roughly 16% of its subscribers (the ERR).
What is TIKVAH-SPORT about?
It is listed in Sports & Fitness, and posts mostly in Tigrinya. The channel describes itself as: “ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469”
Where does TIKVAH-SPORT rank?
By subscribers it is #1 in Sports & Fitness, #3 in 🇪🇹 Ethiopia, #2 among Tigrinya channels, #215 worldwide.
Does TIKVAH-SPORT post ads?
None of its 29 posts in the last 30 days carried an ad label such as #ad or Sponsored. Unlabelled promotions can’t be detected.
Statistics updated 1 hour ago.