EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1
- 24 hours
- −44
- 7 days
- –
- 30 days
- –
- Reactions
- 8
- Reposts
- 1
- Comments
- 0
Subscriber growth
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) has 132,441 subscribers. A typical post is seen by about 3,801 people within a day, an engagement rate of 2.9%.
Daily numbers, last 30 days
| Date | Subscribers | Change | Posts | Avg. post views |
|---|---|---|---|---|
| 18 Nov | 132,441 | −40 | 10 | 1,608 |
| 17 Nov | 132,481 | – | 24 | 3,476 |
Views as a post ages
Average views at each age, posts of the last 30 days.
- 3 h
- 2,108
- 6 h
- 2,755
- 12 h
- 3,152
- 24 h
- 3,799
- 48 h
- 5,429
When it posts
Times in UTC. 54 posts in 90 days.
Recent posts
-
ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዞ በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ሥርዓት መከናወን አለበት - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል:: ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው የሆስፒታሉ ግንባታ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ አሁን ላይ ወደ መጠናቀቂያው ምዕራፍ መድረሱን ገልጸዋል
-
ኢትዮጵያ ለCOP32 ዝግጅት ከተመድ የአካባቢ ፕሮግራም ጋር ያላትን ትብብር እያጠናከረች ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ በቱርክ አንታልያ እየተካሄደ ካለው 31ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP31) ጎን ለጎን ከተመድ የአካባቢ ፕሮግራም (UNEP) ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል:: በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በቀጣይ ለምታስተናግደው 32ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) እየተደረጉ ባሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ በስፋት መክረዋል
-
የአረንጓዴ ምህንድስና ተምሳሌት የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በቢሾፍቱ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው ግዙፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአፍሪካን የአቪዬሽን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የዘመናዊ ምህንድስና እና የአካባቢ ጥበቃ ፍልስፍናን ድንቅ ውሕደት በይፋ እያሳየ ይገኛል:: የክፍለ ዘመኑ ግዙፍ የአቪዬሽን መሠረተ ልማት የሆነው ይህ ታላቅ ፕሮጀክት የኢኮኖሚ ዕድገት እና የተፈጥሮ ጥበቃ ተጣጥመው መጓዝ እንደሚችሉ በተጨባጭ እያረጋገጠ ነው
1,340 views Photo -
የ'ስቶፕ-ኦቨር' (Stopover Tourism) ቱሪዝም ማዕከል እየሆነች ያለችው አዲስ አበባ የእግረ መንገድ ቱሪዝም (Stopover Tourism) ተጓዦች ከመነሻቸው ተነስተው ወደ ሌላ መዳረሻ ሲበሩ በመሸጋገሪያ ሀገር ውስጥ ለጥቂት ሰዓታት ወይም ቀናት ቆይታ አድርገው የመሸጋገሪያውን ስፍራ መስህቦች እንዲጎበኙ የሚያስችል ዘመናዊ የቱሪዝም ዘርፍ ነው:: ይህ አሠራር የትራንዚት መንገደኞችን ወደ ቱሪስትነት በመቀየር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከማስገኘቱም ባለፈ፣ ተጓዦች በአጭር ቆይታቸው ስለ ኢትዮጵያ በቂ ግንዛቤ አግኝተውና ተማርከው ወደፊት ለረጅም ጊዜ ጉብኝት ተመልሰው እንዲመጡ መንገድ ይከፍታል
-
የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር በክልሉ ዕርቅ እና ሰላም ለማስፈን እየሠራ ነው - አቶ ዳሞራ ያህያ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ክልል ባለ አደራ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳሞራ ያህያ የባለአደራ አስተዳደሩ ዋና ዓላማ ዕርቅ እና ሰላም በማስፈን ሕዝቡን ወደ ተረጋጋ ሕይወት መመለስ መሆኑን ገልጸዋል:: በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ትላልቅ ውጤቶች እንደተመዘገቡ እና በተለይም በጸጥታ እጦት ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል
-
የተመድ ልዑካንና አምባሳደሮች በመቐለ የተሃድሶ ማሠልጠኛ ማዕከልን ጎበኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ልዑካንና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቐለ ከተማ የሚገኘውን የተሃድሶ ማሠልጠኛ ማዕከል ዛሬ ጎብኝተዋል:: ከትናንት ጀምሮ በትግራይ ክልል የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ልዑካኑ፣ ከክልሉ ባለአደራ አስተዳደር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል
-
ከኢትዮጵያ ጋር ሁለንተናዊ የትብብር አድማስ በማስፋት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጎልበት እንሰራለን - የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የኢትዮጵያንና የየሀገራቸውን ሁለንተናዊ የትብብር አድማስ በማስፋት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ:: ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከአፍሪካ፣ እስያ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ አውሮፓ እና ካሪቢያን ሀገራት በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ በትናንትናው ዕለት ተቀብለዋል
-
የፌዴራል ሥርዓትን በብዝኃነት ሚዛን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ከሐሳብ ከፍታ አልፎ የሕዝቦችን አብሮነት፣ እኩልነት እና የጋራ ዕድል የሚወስን የሕልውና ጉዳይ ነው:: ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ በገጠሟት ውስብስብ ተቋማዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ፈተናዎች ውስጥ ሆና የብዝኃነት እና የአንድነት ወርቃማ ሚዛንን ለመጠበቅ የምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ትኩረት የሚስብ ነው
-
ኢትዮጵያ ለአዳጊ ሀገራት የአቪዬሽን ትስስርን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አረጋገጠች ኢትዮጵያ ለዳጊ ሀገራት (LLDCs) የአቪዬሽን ትስስርን ለማሻሻል እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት፣ በዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ኮንፈረንስ ጎን ለጎን በተካሄደው የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) የልማት አጋሮች ውይይት ላይ በድጋሚ አረጋግጣለች:: የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) እና ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቶቹን፣ አባል ሀገራትን፣ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣናትን፣ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽንን፣ ቀጣናዊ ድርጅቶችን፣ የዓለም ባንክን፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የልማት ኤጀንሲዎችን፣ ለጋሽ ሀገራትን፣ የኤርፖርት ኦፕሬተሮችን፣ አየር መንገዶችን እንዲሁም የግል ዘርፍ ባለሀብቶችን ጨምሮ ቁልፍ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል
2,940 views 5 Reactions -
ታዳጊ አትሌቶቻችን የኢትዮጵያን የድል ጉዞ የምታድሱ ሀገራዊ ኩራቶቻችን ናችሁ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን በአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንደኝነት እንድታጠናቅቅ ያስቻሉ ታዳጊ አትሌቶችን በአካል አግኝተው አበረታተዋል:: ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አትሌቶቹ በአፍላ ዕድሜያቸው በዓለም መድረክ ባሳዩት ብቃትና ባስመዘገቡት ድል የሀገራቸውን ሰንደቅ በክብር ከፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል
-
ልማት በሰው ልጅ ክብር ሲለካ የአንድ ሀገር ዕድገት እና ብልጽግና የሚለካው ባላት የተፈጥሮ ሀብት እና በምትገነባቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ብቻ አይደለም:: እነዚህ ሀብቶች እና መሠረተ ልማቶች የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት፣ ክብር እና መሠረታዊ ፍላጎት የሚመልሱ ሰው ተኮር ሲሆኑ ብቻ ሀገር በትክክለኛው የብልጽግና ጎዳና ላይ ትራመዳለች
-
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል:: በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 664 ወንዶች፣ 387 ሴቶች እና 35 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 63 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል
-
የብሔር ብሔረሰቦች መስተጋብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መጥቷል -- አቶ ትግሉ መለሰ በኢትዮጵያ በተሠሩ ሰፊ ሥራዎች የብሔር ብሔረሰቦች መስተጋብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ትግሉ መለሰ ገልጸዋል:: የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በመተባበር 21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በማስመልከት ለሦስቱ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥተዋል
-
COP32 እና የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ለሀገራችን ልማትና ኢንቨስትመንት ያለው አበርክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የ32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን በመሰብሰብ አጠቃላይ የሥራ ሂደት መገምገማቸውን ገልጸዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ጉባኤው ለኢትዮጵያ ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፣ COP32 ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ከመሆኑ ባለፈ ሀገራችን የአየር ንብረትና የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳዎቿን የምታራምድበት፣ ዓለም አቀፍ አጋርነቷን የምታጠናክርበት፣ ኢንቨስትመንትን የምትስብበት እንዲሁም ብሔራዊ ጥረቶቿን ወደ ዘላቂ ውጤት የምትለውጥበት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል
-
የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ገጽታና የኢንቨስትመንት መስህብ እየቀየሩ የሚገኙ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ፣ የደመቀ ባህል እና የበለጸገ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ብትሆንም፣ እነዚህን ጸጋዎች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚና የቱሪዝም ገቢ በመቀየር ረገድ የመሠረተ ልማት ውስንነትና የመዳረሻዎች አለመልማት ዓብይ ማነቆ ሆነው ቆይተዋል:: ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥ ያለሙት የኮሪደር ልማት፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ሦስት የተሳሰሩ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች በኢትዮጵያ የልማት ምኅዳር ላይ አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል
-
ብልጽግና ፓርቲ እና የሩስያው ‘ዩናይትድ ራሽያ’ ፓርቲ የተፈራረሙት የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነቱን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ እና የ‘ዩናይትድ ራሽያ’ ፓርቲ ጠቅላይ ምክር ቤት ጸሐፊ እና የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ ቭላድሚር ያኩሼቭ ፈርመውታል:: “ለሕዝቦች ነፃነት!” ከተሰኘው ሩስያ መራሽ የፓርቲዎች የጋራ ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በሞስኮ የተፈረመው ስምምነት፣ ከዓድዋ ድል ጀምሮ የዘለቀውን የኢትዮጵያና የሩስያ ታሪካዊ ወዳጅነት እና በሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ አጋርነት ወደ ላቀ ተቋማዊ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ነው
-
የአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥና ተደራሽ በሆነ መልኩ ሊቀርብ ይገባል - ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ በሚያስፈልገው ደረጃ፣ በተደራሽ መንገዶች እና ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ጥሪ አቀረቡ:: ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በCOP31 ላይ "ከውጥን ወደ ተግባር፡ በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም (GEF)፣ በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ፈንድ (LDCF) እና በልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ (SCCF) አማካኝነት የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ" በተሰኘው የከፍተኛ ኃላፊዎች ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው
-
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማኅበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር በመርካቶ የበጎነት መንደር/በቅጠል ተራ የተገነቡት ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች ከተራ የግንባታ ሥራ በላይ፣ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚቀይሩ፣ የቤተሰቦችን ተስፋ የሚያድሱና የማኅበራዊ ፍትህን በተግባር የሚያረጋግጡ የመደመር መንግሥት ቁርጠኝነት ማሳያዎች ናቸው:: የቤት ችግርን መቅረፍ ማለት የአንድን ቤተሰብ ነገ መገንባት፣ የልጆችን የተሻለ ዕድል ማረጋገጥ፣ የኑሮ ደኅንነትን ማጠናከርና የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ማነቃቃት ነው
-
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ክብር የመለሰው የልማት ጉዞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ እየተከናወኑ ባሉ ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራዎች የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና የኑሮ ጥራት ማሻሻል ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል:: እነዚህ ሁለገብ የልማት እርምጃዎች የከተማዋን ነዋሪዎች ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ከፍ የሚያደርጉ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን እውን እያደረጉ ናቸው
-
በመቐለ ከተማ 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች ለአንድ ወር ሲሰጥ የቆየውን የተሃድሶ ሥልጠና አጠናቀቁ በመቐለ ከተማ ለአንድ ወር የተሃድሶ ሥልጠና ሲወስዱ የቆዩ 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠናቸውን አጠናቅቀዋል:: በትግራይ ክልል ከ47 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ለተሃድሶ ሥልጠና መመዝገባቸው ይታወቃል
Questions about EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
How many subscribers does EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) have?
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) (@EBCNEWSNOW) has 132,441 subscribers as of November 18, 2026.
How many people see a post on EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)?
A typical post gets about 3,800 views within 24 hours, roughly 3% of its subscribers (the ERR).
What is EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) about?
It is listed in News & Media, and posts mostly in Tigrinya. The channel describes itself as: “EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1”
Where does EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) rank?
By subscribers it is #522 in News & Media, #27 in 🇪🇹 Ethiopia, #20 among Tigrinya channels, #1,466 worldwide.
Does EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) post ads?
None of its 54 posts in the last 30 days carried an ad label such as #ad or Sponsored. Unlabelled promotions can’t be detected.
Statistics updated 2 hours ago.