ሰሌዳ | Seleda
- №1 285 в категории «Новости и СМИ»
- №56: 🇪🇹 Эфиопия
- №37 среди каналов на языке «тигринья»
- №3 401 в мире
የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Seledanewsbot
- 24 часа
- −1
- 7 дней
- –
- 30 дней
- –
- Реакции
- 34
- Репосты
- 12
- Комментарии
- 0
Динамика подписчиков
Подписчиков у канала «ሰሌዳ | Seleda»: 53 624. Средний охват поста за сутки около 6 888, вовлечённость 12,8 %.
По дням, последние 30 дней
| Дата | Подписчики | Изменение | Посты | Ср. просмотры поста |
|---|---|---|---|---|
| 18 ноя | 53 624 | −1 | 16 | 5 112 |
| 17 ноя | 53 625 | – | 15 | 6 864 |
Просмотры по возрасту поста
Средние просмотры в каждом возрасте, посты за последние 30 дней.
- 1 ч
- 3 040
- 3 ч
- 4 152
- 6 ч
- 5 166
- 12 ч
- 5 577
- 24 ч
- 6 873
- 48 ч
- 7 688
Когда публикует
Время по UTC. 48 постов за 90 дней.
Последние посты
-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ "ሼባ ማይልስ" የሳይበር ጥቃት እንዳጋጠመው አስታወቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች ታማኝነት እና ማበረታቻ ፕሮግራም በሆነው "ሼባ ማይልስ" የመረጃ ቋት ላይ የሳይበር ጥቃት ማጋጠሙን አስታውቋል። አየር መንገዱ ለደንበኞቹ ባወጣው መግለጫ በዝርዝር እንዳስታወቀው፣ በሲስተሞቹ ላይ የደረሰውን ክስተት "ወሰኑ የጠበበ" ሲል ገልጾታል፤ ይሁን እንጂ ምን ያህል ደንበኞች እንደተጎዱ ወይም ምን ዓይነት የግል መረጃዎች እንደተጋለጡ አልገለጸም። ግሩፑ በሰጠው ማረጋገጫ እስካሁን ባለው ሁኔታ በደንበኞቹ የፋይናንስ መረጃዎች ላይ ጥቃት መድረሱን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም ብሏል። ጉዳዩን በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተለው እንደሚገኝ ገልጾ፣ ከሳይበር ደህንነት አጋሮች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሙሉውን ተፅዕኖ ለመመርመር እና ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል። @Seledadotio @Seledadotio
-
1 ሚሊዮን ብር በታማኝነት የመለሰው ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕውቅና ተሰጠው፡፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምዕራብ ሶሮ ወረዳ የጃቾ ከተማ ነዋሪ አቶ ቶማስ ላምቤ በስህተት ወደ የግል የባንክ ሂሳቡ የገባውን 1 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ በታማኝነት በመመለሱ እውቅና ተሰጠው። ሕዳር 6ቀን 2019 ዓ.ም አቶ ቶማስ የሌላ ሰው ገንዘብ በስህተት ወደ ሂሳባቸው መግባቱን ካወቁ በኋላ ለባለቤቱ መመለሳቸው የታማኝነትና የሐቀኝነት እሴቶችን በተግባር ያሳየ ተግባር ነው። ይህ አርአያነት ያለው ተግባር በማኅበረሰቡ ውስጥ መተማመንንና ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከማጠናከር ባለፈ የሌሎችን ንብረት በአግባቡ መጠበቅና በታማኝነት መመለስ ያለውን ማኅበራዊ ጠቀሜታ ያሳያል። ለዚህም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጃቾ ቅርንጫፍ የተሰጠው የምስጋናና የዕውቅና ሰርተፍኬት በማኅበረሰቡ ውስጥ መልካም የሥነምግባር እሴቶችን ለማበረታታት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሶ የክልሉ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መረጃውን አመላክቷል። @Seledadotio @Seledadotio
-
በሞያሌ ከተማ እየተባባሰ የመጣው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን አፈናቅሎ ሰብዓዊ ቀውስ መፍጠሩ ተገለጸ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል ኃይሎች መካከል በድንበር ከተማዋ ሞያሌ የቀጠለው ውጊያ በርካታ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት እንዲቃጠሉ በማድረግ በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀሉ ተመላክቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተባባሰው ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ ነዋሪዎች ወደ ሰሜን ኬንያ ማርሳቢት ካውንቲ በመሰደድ ላይ መሆናቸውን እና በስደተኛ ካምፖች ውስጥ የምግብ፣ የንጹሕ ውሃ፣ የወተት እና የሕክምና ድጋፍ እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል። የንግድ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ በመስተጓጎላቸው እና የቁም እንስሳት ገበያዎች በመዘጋታቸው የአርብቶ አደር ማኅበረሰቦች መተዳደሪያ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ πλήት መድረሱን የገለጹት ምንጮች፤ ድንበር ተሻጋሪው ግጭት በኬንያ ግዛትም ጭምር ጉዳት ማድረሱን አስታውቀዋል። በሁለቱም ወገኖች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት ሰላማዊ ዜጎችን ለአደጋ ማጋለጡን ተከትሎ፤ የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና የአካባቢው ተወካዮች ግጭቱ በአፋጣኝ ቆሞ በሰላማዊ ውይይት እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍትሔ እንዲበጅለት ጥሪ አቅርበዋል። @Sel...
-
ጥሩ የኡምራ ቆይታን ከእኛ ጋር ያሳልፉ። تقبل الله عمرتكم
-
ደቡብ ኮሪያ የፈተና ኩረጃንና ማጭበርበርን ለሚያጋልጥ ሰው 75 ሺህ ዶላር ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ይህንን ሽልማት ያቀረቡት በዚህ ሳምንት በሚካሄደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ላይ ተፈታኞች የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የፈተና ስርቆት እንዳይፈጽሙ ለመከላከል ነው ተብሏል። ፕሬዝዳንቱ የማጭበርበር ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ ሰዎችን ያጋለጠ ሽልማቱ እንደሚጨምርለት አሳውቀዋል።በተጨማሪም በኩረጃ ውስጥ ተሳትፈው የነበሩ ሰዎች ሌሎች ተባባሪዎቻቸውን በማጋለጥ መረጃ ካቀረቡ ቅጣቱ እንደሚቀንስላቸው ተገልጿል። ደቡብ ኮሪያ በፈተና ላይ የAI መሣሪያዎችን በመጠቀም የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ መጀመሯ ተዘግቧል። ሀገሪቱ ቁጥጥሯን ያጠበቀችው፣ በሀገሪቱ በተከሰቱ የፈተና ማጭበርበር መበራከትን ተከትሎ እና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ አንድ ተፈታኝ የAI ቴክኖሎጂንና ድብቅ ካሜራን በመጠቀም ፈተና መስራቱን ማመኑን ተከትሎ እንደሆነ ብሉምበርግ ዘግቧል። ደቡብ ኮሪያ በዓለም ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ካላቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን፣ የAI ቴክኖሎጂ አጠቃቀሟም ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሷል። @Seledadotio @Seledadotio
-
የብር ዋጋ መዳከም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ገለጸ‼️ ከሐምሌ 2016 ዓ/ም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወዲህ የኢትዮጵያ ብር በሩብ ዓመት ውስጥ ዝቅተኛ የዋጋ መዳከም መመዝገቡን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር አስታውቋል። ማህበሩ እ.ኤ.አ የ2026/27 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚ እና የውጭ ንግድ ዘርፍ አፈጻጸም አስመልክቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርት የብር ዋጋ በ1.2 በመቶ ብቻ መዳከሙን ገልጿል። በዚህም መሠረት የአንድ የአሜሪካ ዶላር ምንዛሬ ከ158.95 ብር ወደ 160.90 ብር ከፍ ብሏል። በንግድ ባንኮች መካከል የነበረው የውጭ ምንዛሬ መግዣ ተመን ልዩነትም መቀራረብ አሳይቷል። ቀደም ሲል በባንኮች መካከል የነበረው የ5.31 ብር ልዩነት በሩብ ዓመቱ ወደ 2.11 ብር ዝቅ ማለቱን ሪፖርቱ አመላክቷል። ሆኖም በይፋዊው እና በጥቁር ገበያ የምንዛሬ ተመን መካከል ያለው ልዩነት ከ12.0 በመቶ ወደ 16.2 በመቶ መስፋቱ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ተግዳሮቶች አሁንም መቀጠላቸውን ያሳያል ተብሏል። በዓለም አቀፍ የሸቀጦች ገበያ ረገድ የወርቅ ዋጋ በ23.4 በመቶ ሲጨምር ፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ንግድ ምርት የሆነው የቡና ዋጋ በ3.9...
-
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል የአየር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ መጀመሩ ተሰማ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል ውስጥ የዝግጁነት እና የቴክኒክ የጦር ልምምድ እያካሄደ መሆኑን ተከትሎ፣ ሕብረተሰቡ የយሮፕላን ድምፆችን ሲሰማ በፍርሃትና በስጋት እንዳይደናገጥ ጥሪ ቀረበ። የሕዝብ ማስጠንቀቂያና የልምምዱ ዓላማ ነዋሪዎች ምንም ዓይነት ስጋትና ጭንቀት ሳይገባቸው መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ይህ ወታደራዊ ልምምድ በአካባቢው መደረጉ የሰሜኑን አቅጣጫ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ለመቃኘት እንዲሁም ከኤርትራ ድንበር በኩል ሊከሰቱ የሚችሉ የትንኮሳ አደጋዎችን ለመመከት እና አጸፋ ለመስጠት ያለመ ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል። የሠራዊቱ የዝግጁነት ምዕራፍ የአየር ኃይሉ በዚህ መልከዓ ምድር አካባቢ እንዲህ ዓይነት ጥልቅ የዝግጁነት እንቅስቃሴዎችን ማድረጉ፣ በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል የሚታዩ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶችንና የጸጥታ ሁኔታዎችን በብቃት ለመቆጣጠር ታቅዶ የሚከናወን መሆኑን የሚያሳይ ነው። @Seledadotio @Seledadotio
-
🎈 በየወሩ 1 ፐርሰንት በመክፈል ብቻ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!!! 💫 የአዲስ አመት ስጦታ ከቴምር ፕሮፐርቲስ!! ✅ገበያ በሚደራባቸው… ⚫️ሳርቤት ⚫️ቡልጋሪያ እና ⚫️ገላን ✅በተመጣጣኝ ዋጋ በእውነተኛ ቅናሽ እና ከወለድ ነጻ አከፋፈል፤ ስርአቱ የሚታወቀው ቴምር ፕሮፐርቲስ 🔔 በ2019 ተጨማሪ ብስራት ይዞ ብቅ ብሏል! 🌟 ነጋዴው በአንድ ጊዜ ክፍያ ወረቱን ሳያጣ የሱቅ ባለቤት የሚሆንበትን እድል!! ሱቅዎን ከነገበያው ለመውሰድ የሚጠበቅብዎት ✅25 በመቶ ቅድመ ክፍያ ✅ለ24 ወራት በየወሩ የሱቁን ዋጋ 1 በመቶ ብቻ መክፈል ነው! ✅ቀሪውን ክፍያ በ4 የግንባታ ምዕራፎች ሳይጨናነቁ ይከፍላሉ! ✅ቴምር የህልምዎን ማረፊያ በአዲስ አበባ አራቱም አቅጣጫ እየገነባ ነው! ☑️ የእርስዎ ትልቁ ህልም ቋሚ አድራሻ ስለሚያስፈልገው ምርጫዎን ብቻ ይንገሩን! በፈለጉት አካባቢና ካሬ ንግድ ሳይጀምሩ የሚያተርፉባቸው ሱቆች አሉን! ☎️ለበለጠ መረጃ 09-88-34-49-12 ይደውሉልን
-
ስልክ ደውሎ ቀጠሮ እስከማስያዝ የደረሰው አዲሱ የጉግል ጄሚናይ አገልግሎት ይፋ ሆነ ! ጉግል ጄሚናይን ከጥያቄ መላሽነት ወደ ሥራ ፈጻሚነት የሚያሸጋግር “Tasks in Gemini” የተሰኘ አዲስ አገልግሎት አስተዋውቋል። ቴክ ክራንች እንደዘገበው አገልግሎቱ በአሜሪካ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ህንድ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በነፃ መቅረብ ጀምሯል። የሚሠራውም በ “Gemini 4 Hydrogen” ሞዴል ላይ ነው ተብሏል። ሀሳቡ ቀላል ነው፤ ብዙ ደረጃዎችን የሚጠይቅ ሥራ ለጄሚናይ ሰጥተው ወደ ሌላ ጉዳይዎ ይሄዳሉ፤ እሱ ደግሞ ከጀርባ ሆኖ ይጨርሳል። ከኢሜይልዎና ከካሌንደርዎ መረጃ ተነስቶ የቀን ሥራዎችን ሊያደራጅ፣ የጉዞ ዕቅድ ሊያዘጋጅ፣ ተደጋጋሚ ምርምር ሊያከናውን ይችላል። አገልግሎቱ ከዚህም ያልፋል። ስልክ ደውሎ ዋጋ ያወዳድራል፣ ምርት መኖሩን ያረጋግጣል፣ ቀጠሮም ያስይዛል። ይህ እድገት የኤአይ ዘርፍ ወዴት እየሄደ እንደሆነ ያሳያል፤ መረጃ ከሚሰጥ ረዳት ወደ ሥራ ፈጻሚ ወኪልነት። ተደጋጋሚ ሥራዎችን በመውሰድ ጊዜ የሚቆጥብ ከሆነ ዲጂታል አገልግሎቶችን የምንጠቀምበትን መንገድ በእጅጉ ሊቀይረው ይችላል። @Seledadotio @Seledadotio
-
በሩሲያ ሲቤሪያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ 19 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ በሩሲያ ሲቤሪያ ክልል ኬሜሮቮ የተከሰተው የሩሲያ ወታደራዊ የካርጎ አውሮፕላን አደጋ 19 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ሩሲያ አን-12 የተሰኘው ይህ ወታደራዊ አውሮፕላን ትናንት ማክሰኞ የተከሰከሰው የዕለት ተዕለት የበረራ ስልጠና ላይ እያለ መሆኑን የገለጸች ሲሆን፣ አደጋው የደረሰው በቴክኒክ ችግር ሳቢያ ሊሆን እንደሚችል የመጀመሪያ ደረጃ ግምቶች ያሳያሉ። የኬሜሮቮ ክልል ገዥ ኢሊያ ሴሬዲዩክ አደጋው የደረሰው ከያጉኖቮ መንደር አቅራቢያ መሆኑን አስታውቀዋል። የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድኖች በፍጥነት ወደ ስፍራው በማምራት በእሳቱ ላይ ቁጥጥር ማድረጋቸውን ገልጸዋል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሩሲያ የኢንጂነሪንግ እና የአቪዬሽን ባለሙያዎች አደጋውን ለማጣራት ምርመራ የጀመሩ ሲሆን፣ አውሮፕላኑ በወቅቱ ጭነት ይዞ ስለመሆኑ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል አን-12 አውሮፕላኖችን የጦር መሳሪያዎችን፣ ሰራተኞችን ለማጓጓዝ እንዲሁም ለፍለጋ እና የማዳን ስራዎች ይጠቀምባቸዋል። @Seledadotio @Seledadotio
-
ደመወዝ አልተከፈለንም በሚል ጦርነቱን አንዋጋም ያሉት የሕወሓት ተዋጊዎች በሱዳን ማመፃቸው ተገለጸ በጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ሠራዊት በብሉ ናይል ክልል ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጋር በሚያደርገው ውጊያ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ፤ ከኢትዮጵያ ሄደው ከሱዳን ሠራዊት ጋር ተሰልፈው የነበሩ የሕወሓት ተዋጊዎች ደመወዝ አልተከፈለንም በማለት ማመፃቸውና ጦርነቱን አንዋጋም ማለታቸው ተመላክቷል። ይህንን ሁኔታ ተከትሎ የሱዳን መንግሥት ኃላፊነት ወስደዋል ያሏቸውን ጄኔራሎች ማሰራቱ የተነገረ ሲሆን፤ ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ የሕወሓት መሪዎችም ተዋጊዎቹ እንዲመለሱላቸው ቢጠይቁም ከጄኔራል አል ቡርሃን በኩል እስካሁን ምላሽ ባለመሰጠቱ ውጥረት መፈጠሩ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት በሱዳን ያሉት ተዋጊዎች ባለመዋጋታቸው እና በሁለቱ አካላት መካከል ባለው አለመግባባት ምክንያት በቀጣናው ተጨማሪ ግጭቶች ሊከሰቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ማደሩ ተመላክቷል። @Seledadotio @Seledadotio
-
ጋዜጠኛ ቤተልሄም ተስፋዬ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ትናንትና እንኳን እንደ ማንኛውም ሰው ስለ ነገ ህይወቷ ስታስብ፣ ስለ ቀኑ ድካም ስታወራ፣ ሳቅና ጨዋታዋን ስታካፍል ነበር። ህይወት ግን እንዲህ ናት፤ ዛሬ አለን ብለን ስናወራ ነገን አናውቀውም። ትናንት በፌስቡክ ገጿ ላይ በአካባቢዋ ባለው የግንባታ ጫጫታ «በእሁዱ እንኳን ማረፍ መሞትም አይቻልም» ስትል የመጨረሻ ቃሏን አሰፍራ ነበር። ያኔ ማን ያውቅ ነበር ይህ ጽሑፍ የመጨረሻ ስንብቷ እንደሚሆን? በቤቷ መታጠቢያ ቤት ውስጥ በአጋጣሚ አዳልጧት በደረሰባት ድንገተኛ አደጋ፤ ጋዜጠኛ ቤተልሄም ተስፋዬ ይህችን ዓለም ለዘላለም ተሰናብታለች። ከሁሉም በላይ ልብን የሚሰብረው ግን የእናትነቷ ነገር ነው፤ 3 ጨቅላ ልጆቿን ትታ በድንገት ማለፏ የሐዘኑን ክብደት የጨመረ ሲሆን፤ ልጆቿ የእናታቸውን ፍቅርና እንክብካቤ በዚህ ዕድሜያቸው ማጣታቸው እጅግ አሳዛኝ ነው። የቀብር ሥነ-ሥርዓቷም ዛሬ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በኮተቤ ካራ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል። ለሦስቱ ልጆቿ፣ ለቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ ፈጣሪ ብርታቱንና መፅናናቱን ይስጣቸው። @Seledadotio @Seledadotio
-
የስልክ ቻርጀር አጠቃቀም ጥንቃቄ ማጣት ለከባድ የእሳት አደጋ እያጋለጠ ነው። በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምንጠቀምበት የሞባይል ስልክ ቻርጀር በተገቢው ጥንቃቄ ካልተጠቀምንበት ለከባድ የእሳት አደጋ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የደህንነት ማሳሰቢያዎች አመለከቱ። የተበላሹ ቻርጀሮች፣ የተቀደዱ ገመዶችና በአግባቡ ያልተያዙ የኤሌክትሪክ ሶኬቶች የእሳት አደጋን ሊያስከትሉ ከሚችሉ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ። በተለይም ጥራታቸው ያልተረጋገጠ ወይም የተበላሸ ቻርጀር መጠቀም የውስጥ የኤሌክትሪክ ክፍሎቹ ከመጠን በላይ እንዲሞቁ ሊያደርግ ይችላል። በተጨማሪም ቻርጀር በሶኬት ውስጥ በደንብ ሳይያያዝ መቅረት፣ የተጎዱ ገመዶችና ሙቀት በሚበዛባቸው ወይም አየር በቂ በማይዘዋወርባቸው ቦታዎች ስልክን ቻርጅ ማድረግ የአደጋውን ስጋት ይጨምራሉ። አደጋውን ለመከላከል ጥራታቸው የተረጋገጠ ቻርጀር መጠቀም፣ የተበላሹ ገመዶችን መቀየር፣ የላሉ ሶኬቶችን ማስተካከልና ቻርጀሮችን ከአልጋ ልብስና ከሌሎች በቀላሉ ከሚቀጣጠሉ ቁሳቁሶች ማራቅ ያስፈልጋል። ቻርጀር እየሞቀ፣ የቃጠሎ ሽታ እየወጣው ወይም ብልጭታ እያሳየ ከሆነም አጠቃቀሙን ወዲያውኑ ማቆም ይገባል። የኤሌክትሪክ እሳት ቢነሳ በውሃ ለማጥፋት መሞከር አደገኛ ነው...
-
ፕሬዝደንቱ በድሮን ስጋት ውስጥ ወድቀዋል ተባለ‼️ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በድሮን ጥቃት ስጋት ውስጥ በመግባታቸው በአስመራ የሚቆዩባቸውን ቦታዎች ያለማቋረጥ እየቀያየሩ እንደሚገኙ የኤርትራው ተንታኝ ዶክተር መሐመድ ኸይር ኦመር ገለጹ። ስጋቱን ለመቀነስም ስልኮችን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እንዳይጠቀሙ መደረጉንና ወደ አዲሃሎ የገጠር መኖሪያቸው የሚያደርጉት ጉዞ መገደቡን ገልጸዋል። @Seledadotio @Seledadotio
-
ደረቅ ሞከረኒ የዋጠው የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ህፃን ህይወት አለፈ‼️ በማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ሸረሮ ደብረ ጽጌ ከተማ ደረቅ ሞኮሮኒ በመዋጡ የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ህፃን ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡ ክስተቱ ቅዳሜ ህዳር5 ቀን 2019 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 ላይ አስ ንጉስ በተባለ ስፍራ አጋጥሟል።የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ለብስራት ራዲዮ እንደገለፁት ህፃኑ በቤት ውስጥ ክዳኑ ተከፍቶ በተቀመጠ እቃ ውስጥ ጥሬ ሞከረኒ አግኝቶ ሳያኝከው በቀጥታ ወደ አፉ በማስገባቱ እንደታነቀ ተገልጿል። በወቅቱ ወላጆቹ ህፃኑ እየተጫወተ እንደሆነ በማሰብ ትኩረታቸውን ሌላ ነገር ላይ እንደነበር የገለጹት ኢንስፔክተር ታምሩ ህፃኑ በመታነቅ የሲቃ ድምፅ ማሰማቱን ተከትሎ ወላጆቹ ደንግጠው ከአፉ ለማውጣትና ወደ ህክምና ተቋም ለማድረስ ጥረት ቢያደርጉም ህይወቱን ማትረፍ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። የህፃኑ ህልፈት በቤተሰቡ ዘንድ ታላቅ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን ክስተቱ በህፃናት አካባቢ የሚቀመጡ መድኃኒቶችን፣ የአልኮል መጠጦችን፣ ጠንካራና ደረቅ ምግቦችን ጨምሮ ህፃናትን ለአደጋ ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮችን አርቆ ማስቀመጥ ይገባል ሲሉ ኢንስፔክተር ታምሩ ባ...
-
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በሥነ-ምግባር ጉድለት የተገኙ 60 ሠራተኞች ላይ እርምጃ ወሰደ። አንድ ሠራተኛ ከሥራ ተሰናቷል፡፡ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥነ-ምግባር ጉድለት በታየባቸው 60 ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱን ቢሮው አስታውቋል፡፡ ከእነዚህም ከባድ ጥፋት የፈጸመ አንድ ሠራተኛ ከሥራ እንዲሰናበት መደረጉንም የተጠቆመ ሲሆን እርምጃው ከዋናው መሥሪያ ቤት እስከ ወረዳ ጽሕፈት ቤቶች ድረስ ያሉ የሥራ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ ተሾመ ኢደቲ ገልጸዋል። በተጨማሪም ጤናማ የሥራ ባህል ለመገንባትና የሙስና ተጋላጭነትን ለመቀነስ ለሠራተኞችና ለግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች ሰጥቷል።ሙስናን የሚፀየፍ የሥራ ባህል ለመፍጠር፣ ለሕዝብ ቅሬታዎች ፈጣንና ፍትሐዊ ምላሽ ለመስጠት ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው አሳስበዋል። በተጨማሪም በተቋሙ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በቴክኖሎጂ ልማት የተጀመሩ ሁሉአቀፍ የሪፎርም ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ በተለይም ቢሮውን ከማዘመንና አገልግሎት አሰጣጥ ከማሻሻልና ለግብር ከፋዩ የሚሰጡ አ...
-
ሕፃን በማገት 1.5 ሚሊዮን ብር የጠየቀው ግለሠብ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ዋለ በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ጠገዴ ወረዳ ሕዳር 1ቀን 2019 ዓ.ም አቶ ዛፉ ጌታቸው የተባለው ግለሠብ ሃፍቴ ይደግ የተባለውን ሕፃን ልጅ በማገት ቤተሰቦቹን 1.5 ሚሊየን ብር መጠየቁ ተገልፆል። የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ክትትል ሕዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም በአለምገነት ቀበሌ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ አጋቹን በቁጥጥር ሥር በማዋል ሕፃኑ ጉዳት ሳይደርስበት ከቤተሠቦቹ ጋር በሰላም መገናኘት መቻሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሚዲያና ኮሙኑኬሽን ዘግቧል። @Seledadotio @Seledadotio
-
ከነገ ጀምሮ ወደ ሽረ መደበኛ በረራ ዳግም እንጀምራለን -የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የቆየውን የሽረ ከተማ መደበኛ በረራ በነገው ዕለት (ማክሰኞ ኅዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም) ዳግም እንደሚጀምር አሳውቋል። አየር መንገዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው መረጃ መሠረት ከነገው የሽረ በረራ መጀመር ባሻገር ወደ ታሪካዊቷ የአክሱም ከተማ የሚደረገውን በረራም በድጋሚ ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል። በዚህም መሠረት የአክሱም ከተማ በረራ ከሰሞኑ ዳግም አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተቋሙ አረጋግጧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ተከስቶ ከነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቐለ፣ ሽረ እና አክሱም ከተሞች ያደርጋቸው የነበሩ መደበኛ በረራዎችን በጊዜያዊነት ማቋረጡ ይታወሳል። ከነዚህ መዳረሻዎች መካከል ወደ ክልሉ መዲና መቐለ የሚደረገው መደበኛ በረራ ከሁለት ሳምንታት መቋረጥ በኋላ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ዳግም መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን የነገው የሽረ በረራ መጀመርና በቅርቡ የሚጀመረው የአክሱም በረራ የክልሉን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ እ...
-
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት ነገ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡- ✅ ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡30 👉 ጥሩ መናፈሻ፣ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል፣ ቱሉ ዲምቱ ማህበር ቤት፣ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚየም (ፕሮጀት 11፣12)፣ ኦልድ ሲቲ (ቦስተር) እና አካባቢው 👉 ኮዬ ፕሮጀክት 18 በከፊል፣ ንፋስ ስልክ፣ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት፣ ኮዬ ፈጬ እና ቱሉ ዲምቱ መሀል፣ ፋንታ አብዱል መር ወፍጮ ቤት አካባቢ፣ ቱሉ ዲምቱ ፈጬ ማርያም፣ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም ጀርባ ይሉ ማህበር ቤቶች፣ ቱሉ ዲምቱ ቴሌ ታወር እስከ ክፍያ ጣቢያው፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ሼዶች እና አካባቢው 👉 ለቡ መብራት፣ ቫርኔሮ አደባባይ በግራ በኩል፣ ለቡ ሙዚቃ ሰፈር፣ ትራኮን ሪልእስቴት፣ ጀሞ 1 ኮንዶሚኒየም በግራ በኩል ያሉ መኖሪያ ቤቶች፣ ጀሞ 1 መብራት፣ መስታውት ፋብሪካ፣ ጀሞ 3 በከፊል፣ ቡና ሜዳ፣ አለምገና በከፊል፣ ፉሪ፣ ካፒታል ሲሚንቶ እና አካባቢው 👉 ዋልያ ብረታ ብረት፣ ወለቴ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ኖክ ማደያ፣ ባለወልድ እና አካባቢው ✅ ከጠዋቱ 5፡00 – 7፡00 👉 መካኒሳ ኢንዱስትሪ መንደር በከፊል፣ ሀና ማርያ...
7 750 просмотров 22 Реакции 15 Репосты -
የመንግስት ሠራተኞች የፈተና አወቃቀርና ክብደት፦ 1. የባህሪ ብቃቶች (30%) ይህ ክፍል 12 የባህሪ ብቃቶች ተቀምጠዋል፦ 1. ታማኝነትና ሥነ-ምግባር 2. የህዝብ አገልግሎት ቁርጠኝነት 3. የመግባቢያ ክህሎት 4. የቡድን ሥራና ትብብር 5. ችግር የመፍታት ችሎታ 6. በውጤት ላይ ያተኮረ አስተሳሰብ 7. በደንበኛ/ዜጋ ላይ ያተኮረ አገልግሎት 8. የለውጥ አስተዳደር 9. የመሪነት ችሎታ 10. የውሳኔ አሰጣጥ 11. የግጭት አስተዳደር 12. ሙያዊነትና ተግሣጽ 2. የቴክኒክ ብቃቶች (50%) ይህ ክፍል 15 የቴክኒክ ብቃቶች ተዘርዝረዋል፦ 1. የፖሊሲ ልማትና ትንተና 2. ዕቅድና ፕሮግራም አስተዳደር 3. ክትትልና ግምገማ 4. የውሂብ ትንተናና ተጨባጭ ማስረጃ አጠቃቀም 5. የቁጥጥርና ፍተሻ ክህሎት 6. የፕሮጀክት አስተዳደር 7. የአደጋ አስተዳደር 8. ሪፖርት አጻጻፍና ሰነድ አዘጋጅነት 9. የመረጃ አስተዳደር 10. አይሲቲና ዲጂታል ክህሎት 11. የፋይናንስ አስተዳደር መሠረታዊ ዕውቀት 12. የምርምርና ትንተና ክህሎት 13. የጥራት አስተዳደር 14. የግዥና ውል አስተዳደር 15. ከዘርፉ ጋር የተያያዘ ልዩ የቴክኒክ ሙያዊ ዕውቀት 3. የሁኔታ ግምገማና የጉዳይ ትንተና (20%...
7 744 просмотров 34 Реакции 109 Репосты
Вопросы о канале «ሰሌዳ | Seleda»
Сколько подписчиков у канала «ሰሌዳ | Seleda»?
У канала «ሰሌዳ | Seleda» (@seledadotio) 53 624 подписчика на 18 ноября 2026 г.
Сколько человек видят пост в канале «ሰሌዳ | Seleda»?
Средний пост набирает около 6 900 просмотров за 24 часа, это примерно 13 % подписчиков (ERR).
О чём канал «ሰሌዳ | Seleda»?
Канал в категории «Новости и СМИ», язык постов: тигринья. Описание канала: «የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Seledanewsbot»
Какое место занимает канал «ሰሌዳ | Seleda»?
По числу подписчиков: №1 285 в категории «Новости и СМИ», №56: 🇪🇹 Эфиопия, №37 среди каналов на языке «тигринья», №3 401 в мире.
Публикует ли канал «ሰሌዳ | Seleda» рекламу?
За последние 30 дней ни один из 48 постов не помечен как реклама (#ad, Sponsored, «Реклама»). Рекламу без пометки определить нельзя.
Статистика обновлена 2 часа назад.